Telegram Group Search
ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን የተሰጠ መግለጫ‼️

ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ የማይማረው ህወሐት ለአራተኛ ዙር በህዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል። የፌዴራልና የአማራ ክልል ክልሉ መንግስታትም በህዝብ ላይ የተቃጣውን የጥፋት ወረራ በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ አበክረን እንጠይቃለን!

የኢትዮጵያ ህዝብ ዘላለማዊ ጠላት የሆነው ወያኔ ህወሐት በህዝብ ትግል ተገፍትሮ ወደ ትግራይ ከተሰበሰበ በኋላ በተደጋጋሚ ወረራ በመፈፀም በህዝባችን ላይ ለጆሮ የሚከብድ ዘግናኝ ግፍ ፈፅሟል። ምንም እንኳን ህወሐት በተደጋጋሚ ጊዜ በቆሰቆሰው ጦርነት የአማራ እና የአፋር ህዝብ በቀጥታ የገፈቱ ቀማሽ ይሁኑ እንጅ ዋና ዓላማው ኢትዮጵያ ሐገራችንን መበታተን እና የፈራረሰች ሐገር መፍጠር መሆኑን በአፈ ቀላጤው በኩል በተደጋጋሚ ተናግሯል።

ይህ የእናት ጡት ነካሽ ቡድን የሐገራችን ደጀን የሆነውን የሰሜን እዝ የመከለከያ ሰራዊት በማጥቃቱ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያጋጠመውን ቁጣ መቋቋም ተስኖት ለሶስተኛ ጊዜ እየተመላለሰ ያደረገው የሐገር ማፍረስ ሙከራ ባይሳካለትም እንኳን አድፍጦ ለጦርነት ከመዘጋጀት ግን ቦዝኖ አያውቅም።

ህወሐት ከጦርነት ውጭ መኖር የማይችል፣ በጦርነት አድጎ በጦርነት ያረጀ ቡድን በመሆኑ በመላው የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ አማፂያንን ከማስታጠቅ አልፎ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመወገን ሐገራችንን የጦር ቀጠና ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ነበር የከረመው። በቀጥታ ከሚደግፋቸው የጥፋት ኃይሎች በተጨማሪ የራሱን ኃይል በማደራጀት የሰርጎ ገብ ኃይል እየላከ ህዝባችንን ሲረብሽ መክረሙ ሳያንሰው በአሁኑ ሰዓት በራያ በኩል ቀጥተኛ የሆነ ጥቃት በህዝባችን ላይ ለአራተኛ ጊዜ ወረራ ከፍቶ ይገኛል።

ኋላ ቀርነት እና ግትርናት ዋና መገለጫው የሆነው የጥፋት ቡድን የሚሊዮኖችን ህይዎት በቀጠፈውና ከተደጋጋሚ ስህተቱ ባለመማር ዛሬም ለሌላ ዙር እልቂት ተዘጋጅቶ በህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍቷል።

በህዝቦች እኩልነት እና በብሔረሰቦች መብት ፈፅሞ የማያምነው ህወሐት እኔ የማልገዛት ኢትዮጵያ ተረጋግታ መኖር የለባትም የሚል ያልተገራ ክፉ አመሉን በተደጋጋሚ አሳይቷል። በዚህም እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እኩልነትን ፈፅሞ እንደማይሻ አረጋግጧል።

ለህዝባችን የሚከተሉትን መልዕክቶች እናስተላልፋለን

1. ምንም እንኳን አሸባሪው እና ተስፋፊው ወያኔ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጠላት ቢሆንም ፣ በተለይ የአማራ ህዝብ የቡድኑ ወረራ ቀጥተኛ ሰለባ እና ገፈት ቀማሽ በመሆኑ ጦርነቱን የመመከት ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በሁሉም አካባቢዎች የሚገኘው ሕዝባችን ካለፈው የጥፋት ግዜ በመማር ከታሪካዊ ጠላቱ የሚሰነዘርበትን ወረራ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት እንዲመክት፣

2. ህዝባችን ከወያኔ ትጥቅ አስፈች ፕሮፖጋንዳ ራሱን እንዲጠብቅ እና ከዚህ ታሪካዊ ጠላት የሚመጣን ማንኛውንም ውዥንብር ጆሮ እንዳይሰጥ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የወገን ኃይሎች ለወያኔ የሚያሳዩትን የተለሳለሰ የባንዳነት መንገድ ህዝባችን ፈፅሞ እንዳያዳምጥ እና እንዲህ ያሉትን ቡድኖች አጥብቆ እንዲታገል፣

3. የአማራ እና የአፋር ህዝብ የጦርነቱ ዋና ገፈት ቀማሽ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኃይሎች የሚፈልጉትን ሁሉ በማቅረብ ከሐገሩ ጎን እንዲቆም

4. ህዝባችን ይህን ታሪካዊ ጠላት በመቅጣት የተለመደ ጀግንነቱን እንዲወጣ ስንል ጥሪ እያቀረብን፤ በተለይ መንግስት በህዝባችን ላይ ለአራተኛ ጊዜ እየተፈጸመ የሚገኘውን ወረራ በዝምታ የሚመለከት ከሆነ፤ ህዝባችን ስርአትን አምኖ ችግሮች ሁሉ በህግ አግባብ ይፈታሉ የሚል ቀናኢነቱ ማታለያ ሆኖ ከዋለ፤ ይህ በራያ ብቻ የማይቆም ይልቁንም የሁሉ ነገር መፍረሻና ማፍረሻ እንዲሆን መንግስት የፈቀደ መሆኑን ታሪክ የሚመዘግበው ሀቅ ይሆናል።

5. በህወሐት ችግር የአማራና የትግራይ ህዝቦች እንዲሁም መላ ሀገሪቱና ቀጠናው ችግር ውስጥ እየወደቀ በመሆኑ ይህ በአስቸኳይ እንዲቆም እያሳሰብን በተለይ የፌዴራሉ መንግስትና የአማራ ክልል መንግስት በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ የሚገኘውን ወረራ በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ አበክረን እንጠይቃለን!

ሚያዝያ 07/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ

@Esat_tv1
@Eaat_tv1
በኮሪደር ልማት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት ሆኑ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች እየተከናወኑ በሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ምክንያት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጋቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት፡-

ከደጃች ውቤ በአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

ከባሻወልዴ ችሎት በቱሪስት ሆቴል ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

ከዳኑ ሆስፒታል እስከ ቱሪስት ሆቴል በመውጣት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

ከአራዳ መስተዳደር ወደ ዳኑ ሆስፒታል መውረጃ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አሽከርካሪዎች መጠቀም እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እየተከናወኑ ባሉ የልማት ሥራዎች ምክንያት ለአጭር ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በጥብቅ መከልከሉንም ነው ፖሊስ ያሳሰበው፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
Niya Online payment ‼️

የተለያዩ እንደ SAT እና USMLE ያሉ የውጭ ፈተናዎችን ክፍያ ለመፈጸም ለ Scholarship application fee ለመክፈል ከ Alibaba, Amazon እና የመሳሰሉ የኦንላይን ገበያዎች ላይ ክፍያ ለመፈጸም እንዲሁም ለሌሎች ማንኛውንም በ online የሚከፈሉ ክፍያዎች ለመክፈል ፈልገው ተቸግረዋል❓

እንግዲያውስ እኛ ጋር መፍትሄ አለ!

በVisa card, Mastercard ወይም በ Payoneer እንደራስዎ ሆነን ክፍያዎን እንፈጽምሎታለን!

- በ ቴሌግራም  አድራሻችን 👉@StraightouttaNazreth
-በ ስልክ ቁጥራችን 👉+251934729413 ይደውሉ

Niya online payment
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶውን ማስመለስ መቻሉን አስታወቀ‼️

የኢትዯጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶ የሚሆነውን ማስመለሱን አስታውቋል።ባንኩ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ በተጠቀሰው ዕለት በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801 ሚሊዮን 417 ሺህ 747.81 ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር መገለፁ ይታወሳል።

ከተወሰደው ገንዘብ 762 ሚሊዮን 941 ሺህ 341 ብር ማስመለስ መቻሉን ባንኩ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን 38 ሚሊዮን 474 ሺህ 938 ብር የማስመለስ ስራ እንደሚቀጥልም ባንኩ ገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
Photo
ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ‼️

የክልሉ መንግሥት ፥ " ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል " ሲል ከሷል።

" ህወሓት የአማራ ክልል ተማሪዎችን መማሪያ መጽሐፍ እንደ ሰበብ ተጠቅሞ በይፋ ጦርነት ማወጁና መቀስቀሱ ይታወቃል " ሲል አስታውሷል።

የአማራ ክልል መንግሥት ህወሓትን " የመላ ኢትዮጵያ ጠላትና የደኅንነት ስጋት " እንደሆነ ገልጾ " ባለፉት 3 ዙሮች ከተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት ትምህርት ሊወስድ ይችል ይሆናል በሚል ጭላንጭል ተስፋ የፌዴራል መንግሥት እጅግ እልህ አስጨራሽ ትዕግስት ተላብሶ ውይይቶች እንዲካሄዱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል " ብሏል።

" የአማራ ክልል መንግሥትም በተደጋጋሚ ከትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር ጋር በፌዴራል መንግሥት አማካኝነት ውይይት ለማድረግ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም ህወሓት ይህን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል " ሲል ገልጿል።

" ህወሓት ወረራ የፈፀመባቸው ፦
- የራያ አላማጣ፣
- ራያ ባላ፣
- ኦፍላ፣
- ኮረምና ዛታ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አካባቢዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት በነበሩ አሥተዳደራዊ መዋቅርና አደረጃጀት በኀይል ጠቅልሎ ከመውሰድ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈፀም ድረስ አሰቃቂ ጥፋት የፈፀመባቸው አካባቢዎች  ናቸው " ብሏል።

" ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ህወሓት በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የከፈተውን አሰቃቂ ጥቃት ተከትሎ ከተቀሰቀሰው ጦርነት በኃላ አካባቢዎቹ በጉልበት ተገፎባቸው የነበረውን ራሳቸውን የማሥተዳደር ነጻነት መቀዳጀት እንደቻሉ " የአማራ ክልል መንግሥት ገልጿል።

በኃላም የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መፈረሙን ፤ ህወሓት ግን ስምምነቱን በማክበር በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የድርሻውን ከመወጣት ይልቅ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የተለያዩ ጥፋቶችን ሲፈጽም እንደቆየ አመላክቷል።

" አሁንም እየፈጸመ ይገኛል " ብሏል።

የአማራ ክልል መንግሥት ፥ ህወሓት ደም አፋሳሽ የሆነ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀብ እና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲያከብር አሳስቧል።

" በአጭር ጊዜ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ " ሲል ጠይቋል።

" ይህ የማይሆን ከሆነ የአማራ ክልል መንግሥት እና ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ በመሆን ሀገርን ከማፍረስ መታደግናረ ሕዝባችንንም ከጥቃት ለመከላከል እንገደዳለን " ሲል አስጠንቅቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@Esat_tv1
@Esat_tv1
አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት ኢራን ላይ ማዕቀብ ለመጣል ዝግጅት ጀመሩ‼️

ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ኅብረት፤ እስራኤል ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ኢራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል እየተሰናዱ ነው።የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ጃኔት የለን “በሚቀጥሉት ቀናት” እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊስ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ደግሞ ኅብረቱ ማዕቅብ ለመጣል እየሠራ መሆኑን ገልጠዋል።እስራኤል አጋሮቿ የኢራን የሚሳዔል ፕሮግራም ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ጠይቃለች።

የተባበሩት መንግሥታት የኢራን የሚሳዔል ፕሮግራም ላይ የጣለው ማዕቀብ ባለፈው ጥቅምት ጊዜው አብቅቷል።እኒህ ማዕቀቦች የሚጣሉት የኢራንን የኒውክሌር ፕሮግራም ለመግታት ነው የሚሉ ሐሳቦች ከፖለቲካ ተንታተኖች ዘንድ ይሰማሉ።አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ኢራን ላይ የተለያዩ ማዕቀቦች ከዚህ ቀደም መጣላቸው አይዘነጋም።የእስራኤል ጦር ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ሌተናንት ጄኔራል ሄርዚ ሀሌቪ ባለፈው ሰኞ በሰጡት አስተያየት ኢራን ያደረሰችው ጥቃት ምላሽ ሳያገኝ አያልፍም የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር።

ኢራን ባለፈው ቅዳሜ ለመጀመሪያ ጊዜ እስራኤል ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ባደረሰችበት ወቅት 300 ሚሳዔሎችና ድሮኖች ከራሷ ክልል፣ ከኢራቅ፣ ሶሪያ እና የመን አስወንጭፋለች።አብዛኛዎቹ ሚሳዔሎች እና ድሮኖች በእስራኤል እና አጋሮቿ ዒላማቸውን ሳይመቱ እንዲከሽፉ ተደርገዋል።ቴህራን እንዳለችው ጥቃቱን የሰነዘረችው እስራኤል፤ ሶሪያ በሚገኘው ቆንስላዋ ላይ ጥቃት አድርሳ 13 ሰዎችን ለገደለችበት ጥቃት አፀፋውን ለመመለስ ነው።

እስራኤል ለደረሰባት ጥቃት እስካሁን ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጠችም። በምትኩ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኢራንን ለማሽመድመድ እየሠራች ትገኛለች።እስራኤል 30 የሚሆኑ አጋር ሀገሮች የኢራን የሚሳዔል ፕሮገራም ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ጠይቃለች።አልፎም እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ኢስላሚክ ሪቮሎሺናሪ ጋርድ ኮር የተባለው የኢራን ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ኃይል ሽብርተኛ ተብሎ እንዲፈረጅ ጠይቃለች። አሜሪካ ከዚህ ቀደም ቡድኑን ሽብርተኛ ብትልም ዩኬ ይህን ከማድረግ ተቆጥባለች።

ማክሰኞ ዕለት ንግግር ያደረጉት የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሚኒስትር የለን “በሚቀጥሉት ቀናት ኢራን ላይ ማዕቀብ እንደምንጥል ይጠበቃል” ብለዋል።ሚኒስትሯ አክለው ኢራን ወደ ውጭ የምትልከው ነዳጅ “ምናልባት የምናየው ይሆናል” ካሉ በኋላ “ኢራንም አሁንም በግልፅ ነዳጅ እየሸጠች ነው፤ ስለዚህ ጉዳይ የምናደርገው ነገር ይኖራል” ሲሉ ማዕቀቡ ምን ላይ እንደሚያተኩር ጠቁመዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ዱባይ በጎርፍ ተጥለቀለቀች‼

በዱባይ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መጠን ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ ከተማዋ በጎርፍ ተጥለቅልቃለች።

ጎርፉን ተከትሎ የዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያን ጨምሮ የከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች ከባድ ጎርፍ እያስተናገዱ መሆኑ ተገልጿል።

በተለይም ከዚህ ቀደም በርከታ በረራዎችን ሲያስተናግድ በነበረው የዱባይ አየር መንገድ በረራዎች ተስተጓጉለዋል።

ነፋስ የቀላቀለው ከባድ ዝናብ በኦማን ተከስቶ 18 ሰዎች ህይወታቸው ካለፈ በኋላ አሁን ደግሞ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና በባህሬን ጉዳት እያስከተለ እንደሚገኝ የአልጀዚራ ዘገባ ያመለክታል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ አካሂዶ በሁለት ጉዳዮች ውሳኔ አሳልፏል‼️

ውሳኔ ከተላለፈበት አንዱ ጉዳይ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ነው።

ምክር ቤቱ ፥ " በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርከቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዋል " ብሏል።

" ሆኖም እነዚህ አሰራሮች ፦
- በእውኀት፣
- በዕርቅ፣
- በምህረት እና በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብአዊ መብት ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም " ሲል ገልጿል።

በመሆኑንም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቀረቡን አስረድቷል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
የዉጪ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ከነዳጅ በስተቀር በሁሉም የንግድ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ ተፈቀደ‼️

መሰረታቸውን በዉጪ ያደረጉ ባለሃብቶች በችርቻሮ እና በጅምላ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ፍቃድ መሰጠቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን እና የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጋራ አስታውቀዋል።

ከጅምላ ንግድ ጋር ተያይዞ ከማዳበሪያና ከነዳጅ ጅምላ ንግድ በስተቀር በሁሉም አይነት የጅምላ ንግድ መስኮች መሰማራት ይችላሉ ተብሏል በዚህም በጥሬ ቡና፣ በቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ጥራጥሬ፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የደን ውጤቶች እና የቁም እንስሳት የመላከ የወጪ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ነዉ የተፈቀደው ።

ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልለው የቆዩ የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች አሁን ደግሞ ለውጭ ባለሃብቶች ከፍት እንዲሆኑ መደረጉ ነዉ ለማወቅ የተቻለው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረች‼️

እስራኤል ኢስፋሃን በተባለ የማዕከላዊ አራን አካባቢ ባሉ ወታደራዊ ካምፖች ላይ በድሮኖች ጥቃት መሰንዘሯን አለማቀፍ ሚድያዎች እየዘገቡት ነው፡፡

ይህን ተከትሎ ኢራን የጸረ-ሚሳኤል መከላከያ ማስወንጨፏንና የተተኮሱባትን ሦስት ድሮኖች መታ መጣሏን አስታውቃለች።

ኢስፋሃን የኢራን አየር ኃይል እና የኒዩክሌር ጣቢያ የሚገኝ ከተማዋ ሲሆን በአካባቢው የተሰማው ፍንዳታ ኢራን ያስወነጨፈቻቸው የጸረ ሚሳኤል መከላከያ መሆኑን አገሪቱ ባወጣችው መረጃ ገልጻለች።

የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ የአየር በረራዎች ተስተጓጉለው እንደነበርና በአሁኑ ሰዓት በረራ መጀመሩን እንዲሁም አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን የአልጃዚራ ዘገባ አመላክቷል።

በፈረንጆቹ ሚያዝያ 1 ቀን እስራኤል ሶሪያ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ላይ ባደረሰችው ጥቃት 13 ዜጎቿ መገደላቸውን ተከትሎ በእስራኤል ላይ ባሳለፍነው ቅዳሜ 300 ሚሳኤልና የድሮን ጥቃት ማድረሷ ይታወሳል።

ለኢራን ጥቃት እስራኤል አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታ እንደነበርም የሚታወስ ነው።
የሁለቱ አገራት የሰሞኑ ግጭትን ተከትሎ አገራት ዜጎቻቸውን ወደ እስራኤል እንዳይጓዙ እያስጠነቀቁ ነው።

ከስውር ጦርነት አልፎ ወደ ይፋዊና ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ የገባው የሁለቱ አገራት የሰሞነኛ ፍጥጫ በቋፍ ላይ የነበረ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ወደለየለት ጦርነት እንዳይከተው ተሰግቷል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
የአማራ ክልል ለ1 ሺህ 460 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ‼️

የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም ይቅርታውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሠጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በክልሉ የይቅርታ አሠጣጥ መመሪያዎች መሠረት በበጀት አመቱ ሁለተኛ ዙር በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን አንስተዋል።

በይቅርታው በማረሚያ ቤት ቆይታቸው በመታረምና በመታነፅ አርአያነት ያሳዩ፣ ከተበዳይ ወገኖች ጋር እርቅ የፈፀሙ፣ አስፈላጊውን ካሳ የከፈሉ እና ለማህበረሠቡ የወንጀልን አስከፊነት እንደሚያስተምሩ የታመነባቸው 1 ሺህ 431 ወንድ እንዲሁም 29 ሴት ታራሚዎች ይቅርታ እንደተደረገላቸው ገልፀዋል።

በተጨማሪም መስተዳድር ምክር ቤቱ የተሠጣቸውን ይቅርታ ባለመጠበቅ ሌላ ወንጀል ፈፅመው በቻግኒ ማረሚያ ቤት የሚገኙ አምስት ግለሠቦችን ይቅርታ መሰረዙንም ኃላፊው ጠቁመዋል።

የህግ የበላይነት የሁለንተናዊ ለውጥ እና ለዘላቂ ሠላም መሠረት ነው ያሉት ኃላፊው፤ በክልሉ በሚታየው የፀጥታ ችግርና በሌሎችም አጋጣሚዎች ከማረሚያ ቤት የወጡ ፍርደኞች እና ጉዳያቸው በሂደት ላይ የነበሩ ታራሚዎች ተመልሠው በህግ እንደሚዳኙም ገልፀዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ናቸው‼️

የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ሩጫው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
    
በውድድሩ ወቅት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡

ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም  መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገውና የአዲስ አበባን ዋና ዋና መንገዶችን የሚያካልለው የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

ከዚህ ቀደም በርካታ ህዝብ በብዛት የተሳተፈባቸው ተመሳሳይ  ሩጫዎች በሰላም መጠናቀቃቸውን ያስታወሰው ፖሊስ በመጪው እሁድ  በከተማችን የሚካሔደው የሩጫ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ሾል መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 

የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራ ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ  ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

መነሻውን ከመስቀል አደባባይ በማድረግ   በለገሃር ፣ ሜክሲኮ አደባባይ ፣ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ፣ ቄራ ፣ ጎተራ ማሳለጫ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ጥላሁን አደባባይ አድርጎ  መዳረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ውድድር  ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ
•  ከመገናኛ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ
•  ⁠ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል
•  ⁠ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ አጎና መስቀለኛ
•  ⁠ከጎርጎሪዎስ አደባባይ ወደ ጎተራ
•  ⁠ከጎተራ ሼል ወደ ጎተራ
• ⁠ከማሞ ማቋረጫ ወደ ጎተራ
•  ⁠ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
•  ⁠ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ቄራ በረት
•  ⁠ከመካኒሳ አቦ አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
•  ⁠ከካርል አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
•  ⁠ከልደታ ፀበል ወደ ኤዩ መብራት
•  ⁠ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደኤዩ መብራት
•  ⁠ከኦርቢስ መታጠፊያ/ጮራጋዝ/ መስቀለኛ ወደ ሲጋራ ፋብርካ
•  ⁠ከጠማማ ፎቅ ወደ ጥይት ፋብርካ
•  ⁠ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ወደ ገነት መብራት
•  ⁠ከከፍተኛ ፍ/ቤት /ባልቻ ሆስፒታል/ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
•  ⁠ከአረቄ ፋብርካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
•  ⁠ከሠንጋ ተራ 40/60 መስቀለኛ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት
•  ⁠ከበድሉ ህንፃ ወደ ቴሌ ባር
•  ⁠ከብሔራዊ ቲያትር መብራት ወደ ለገሃር መብራት
•  ⁠ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት
•  ⁠ከብ/ቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
•  ⁠ከኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ  እንደሚሆኑ እና ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ውድድሩ ፍፃሜ ድረስ ጎፋ ማዞሪያ ድልድይ ፣ በቅሎ ቤት ድልድይ እና ጥላሁን አደባባይ ድልድይ አካባቢ ለረዥም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍጽም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል፡፡  በየአካባቢው ለተመደቡ የትራፊክ ፖሊስ እና የፀጥታ አካላት ተባባሪ በመሆን የሚሰጡትን ትዕዛዝ አሽከርካሪዎች  በማክበር የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ አዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
በ41 ዓመቱ ፈጣኑን የማራቶን ሠዓት ያስመዘገበው አትሌት‼️

🗣ቀነኒሳ በቀለ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን በተካሄደው የማራቶን ውድድር ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ከ2019 ወዲህ ፈጣኑን ሠዓት በማስመዝገቡ አድናቆት ተችሮታል፡፡

አትሌት ቀነኒሳ የዛሬውን የለንደን ማራቶን ውድድር 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡

የዓለም አትሌቲክስም አትሌቱ የገባበት ይህ ሠዓት ከ2019 ወዲህ ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ዘንድ ሲመዘገብ የመጀመሪያው መሆኑን በመግለጽ አድናቆቱን ገልጿል፡፡

አትሌቱ ባለፈው የፈረንጆቹ ታኅሣስ ወር ላይ በቫሌንሲያ ማራቶን ውድድር 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ19 ሠከንድ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን በለንደን ማራቶን ደግሞ ይህን ሠዓት በአራት ሰከንድ ዝቅ በማድረግ አሻሽሎታል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ያለአግባብ ከተወሰደው ብር 96 ነጥብ 3 በመቶው ተመልሷል‼️

🗣የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ባሳለፍነው መጋቢት ወር ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ባጋጠመ ችግር ምክንያት 801 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ያለአግባብ መወሰዱን ባንኩ አስታውሷል፡፡

ከዚሁ የገንዘብ መጠንም እስከ አሁን 96 ነጥብ 3 በመቶ (771 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር) ተመላሽ መደረጉን የባንኩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ቀሪውን ያለአግባብ የተወሰደ ብር የማስመለስ ሥራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተመላከተው፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
2024/05/08 18:47:39
Back to Top
HTML Embed Code: